Search

“ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ” ዓለም አቀፍ ፎረም በመጋቢት ወር ይካሄዳል

ሰኞ ታኅሣሥ 13, 2018 32

ዓለም አቀፍ የቢዝነስ መሪዎች የሚሳተፉበት “ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ” ፎረም በመጋቢት ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።

በ4ኛው “ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ” ፎረም ከ700 በላይ ዓለም አቀፍ የቢዝነስ መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና አጋር የልማት ድርጅቶች እንደሚሳተፉበት ኮሚሽኑ ለኢቢሲ የላከው መረጃ ያመለክታል።

ከ3 ወራት በኋላ የሚካሄደው ፎረም አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንደሚያስተዋውቅ ኮሚሽኑ ጠቁሞ፤ ይህም የውጭ ባለሀብቶች አዳዲስ እና የማስፋፊያ የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል ነው ብሏል።

ፎረሙ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ለማዘመን እየተገበረችው ባለው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዋ በለየቻቸው 5 ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተመላክቷል።

አምራች ኢንዱስትሪ፣ ግብርና፣ አይሲቲ፣ ማዕድን እና ታዳሽ ኃይል፤ ቱሪዝም እና አገልግሎት ዘርፎች ያሏቸውን አማራጮች በፎረሙ በስፋት እንደሚተዋወቁም ተገልጿል።

ፎረሙን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የልማት አጋሮች በትብብር ያሰናዱታል።

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #Investment #InvestInEthiopia