በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጀመርያ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ አንጎላን 2 ለ 1 በማሸነፍ አጀማመሯን አሳምራለች፡፡
በማራካሽ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኦስዊን አፖሊስ እና ሌይል ፎስተር የደቡብ አፍሪካን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ ሾው የአንጎላን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡

ቀደም ብሎ በተካሄደ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ጨዋታ ማሊ ከዛምቢያ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል፡፡
ላሲን ሲኒያኮ ለማሊ ፓትሰን ዳከ ደግሞ ለዛምቢያ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
ምድብ አንድን ትላንት ኮሞሮስን 2 ለ 0 ያሸነፈችው ሞሮኮ በሦስት ነጥብ እየመራች ትገኛለች፡