Search

የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር

ማክሰኞ ታኅሣሥ 14, 2018 145

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ የኬንያ ፕሬዚደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በውይይቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አመልክተዋል።
ይህም በሰላም እና መረጋጋት፣ ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።