Search

የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀሰን ዓሊ ከ27 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሓሙስ ታኅሣሥ 16, 2018 128

የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሀሰን ዓሊ 27 ዓመታት የውጭ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

አቶ ሀሰን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣አቶ ሀሰን ዓሊ ወደ ሦስት አሥርተ ዓመታት ከሚደርስ ጊዜ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የተቀበልኳቸው በታላቅ ክብር ነውብለዋል።

የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሀሰን ዓሊ የክልሉ መንግሥት ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ግለሰቦች መካከል አንዱ እንደሆኑም ጠቅሰዋል።

በሁሉም ደረጃዎች ለተወጡት ኃላፊነት እንዲሁም ለአገልግሎታቸው በራሳቸው እና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ስም አመስግነዋል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በተለያዩ ምክንያቶች ከሕዝባቸው ርቀው የቆዩ የሕዝብ ልጆችን በጥንቱ እሴት መሠረት ወደ ቀዬአቸው ለማቅረብ ፍላጎት እና ቁርጠኝነቱ ያለው መሆኑን አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ አጋጣሚ አረጋግጠዋል።

አቶ ሀሰን ዓሊ 1984 . ጀምሮ እስከ 1987 . ድረስ የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው አገልግለዋል።

#ebcdotstream #EBC #Ethiopia