Search

ምቹ የኢንቨስትመንት ምሕዳር የፈጠረው የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ

እሑድ ታኅሣሥ 19, 2018 381

የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለሕንድ ባለሃብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ምሕዳር መፍጠሩን በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ ገለጹ።

አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ካላቸው ሀገራት መካከል ሕንድ አንዷ ናት።

የሕንድ ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ትኩረት በሰጠቻቸው የጤና፣ ግብርና፣ ጨርቃ ጨርቅ እና ሌሎች መስኮች 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ኢንቨስትመንት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ይህም በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በዲጂታላይዜሽን የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል።

በቀጣይም የሕንድ ባለሃብቶች የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል በመጠቀም በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ምርታማነት ላይ በስፋት እንዲሳተፉ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያና የሕንድ ታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ስታራቴጂያዊ አጋርነት መሸጋገሩም የሕንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

#EBCdotstream #Ethiopia #homegrowneconomicreform #investment #India