Search

የሐረር የኮሪደር ልማት ሥራዎች የሕዝቡን መሠረታዊ ፍላጎቶች የሚያሟሉ ናቸው - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ረቡዕ ታኅሣሥ 22, 2018 113

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በሐረር ከተማ እየተሠሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፤ በሐረር ከተማ የዘመናት ጥያቄዎችን ምላሽ የሚሰጡ እና ለመጪው ትውልድም መሠረት የሚጥሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ።
እነዚህ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ቀደምት ሥልጣኔ የሚመጥኑ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል።
በተጨማሪም በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች የሚመልሱና የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በተለይም ሰፊና ምቹ የተሽከርካሪ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የመንገድ ዳር መብራቶች እና የዕድሳት ሥራዎች፤ ዜጎች የእረፍት ጊዜያቸውን በምቾት እንዲያሳልፉ የሚያግዙ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች መሆናቸውን አስረድተዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ