Search

ዮሐንስ ሳሕሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተመረጡ

ሓሙስ ታኅሣሥ 23, 2018 133

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በመምረጥ ውሳኔ አሳልፏል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ በአሁኑ ወቅት የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ታዳጊ እና ዋናው ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት ከመምራታቸው በተጨማሪ ፌዴሬሽኑን በቴክኒክ ዳይሬክተርነት አገልግለዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኙ እየሰሩበት ከሚገኘው ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር ንግግር ካደረገ በኋላ የውል ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #EFF #NationalTeam #Coach