የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
በስብሰባው ላይ ሁለቱም ወገኖች በኢትዮጵያ እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን የግንኙነት መስኮች ላይም የበለጠ ተቀራርበው ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሚኒስትር ዴኤታው ጋር የጋራ ፍላጎት ባላቸው ቀጣናዊ የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያም ሀሳብ ተለዋውጠዋል።