የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እና ቻይና የ2026 የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የጋራ ፕሮግራምን ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አደረጉ።
ፕሮግራሙ ይፋ ሲደረግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ፣ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በቻይና እና አፍሪካ መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንደሚያሳድግ ለታመነበት ፕሮግራም የራሱ መለያ (ሎጎ ) ይፋ ሆኗል።
በሞላ ዓለማየሁ