ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ ስደርስ ክቡር ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ አቀባበል አድርገውልኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ውይይታቸውም በጂኦፖለቲካል ጉዳዮች፣ በቀጣናዊ ሰላም እና ፀጥታ ብሎም የሁለትዮሽ ትብብራችንን በተለይም በንግድ፣ ሎጂስቲክስ እና የልማት ሥራዎች በምናጠናክርበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጽ አስፍረዋል።

ይኽም ለሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትስስር እና የጋራ ብልፅግና ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያመለክት ነው ብለዋል።