የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የሚታደሙበትና በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች፣ የጥምቀት በዓል በሁሉም ስፍራዎች ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀና ፍፁም ባማረ መልኩ እንዲከበር እየተከናወኑ ባሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም አጠቃላይ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን ከንቲባዋ ከውይይቱ በኋላ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል እንደ ሌሎች ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ሁሉ በታላቅ ድምቀትና በሰላም እንዲከበር የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባ አዳነች አረጋግጠዋል።
#EBC #EBCDotstream #Timket #Epiphany #EOTC #AddisAbaba