ኢትዮጵያ ከቻይና ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን ግዙፉን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ (World Internet Conference - WIC) በመጪው መስከረም ወር በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ዝግጅቷን እያጠናቀቀች መሆኑ ተገልጿል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የWIC ምክትል ዋና ፀሐፊ ሚስተር ሊያን ሃኦን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ምክክሩ በዋናነት ኮንፈረንሱ በስኬት እንዲከናወን በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ያተኮረ እንደነበር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
🔥 ኮንፈረንሱ ለኢትዮጵያ ያለው ፋይዳ
ይህ ኮንፈረንስ ለሀገራችን በርካታ ጥቅሞችን ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል፦
✅ የቴክኖሎጂ ሽግግር፡ እንደ Google፣ NVIDIA፣ IBM እና Alibaba ያሉ ከ200 በላይ ዓለም ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሳተፉበት በመሆኑ ለኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዕድገት ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
✅ ኮንፈረንስ ቱሪዝም፡ አዲስ አበባን የዓለም አቀፍ ስብሰባዎች መዳረሻ (Hub) የማድረግ ራዕይን ያሳካል።
✅ ኢንቨስትመንት፡ የዓለም አቀፍ የዘርፉ ተዋናዮችና ምሁራን በሚሳተፉበት በዚህ መድረክ አዳዲስ የኢንቨስትመንት በሮች ይከፈታሉ።
👉 ስለ ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ (WIC) በጥቂቱ
ከ2012 ጀምሮ በየዓመቱ በቻይና ሲካሄድ የቆየው ይህ ታዋቂ ኮንፈረንስ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ውጭ እንዲካሄድ ሲወሰን ኢትዮጵያ መመረጧ የሀገራችንን ዲፕሎማሲያዊ ተቀባይነትና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያመጣችውን እመርታ የሚያሳይ ነው።
ዶ/ር በለጠ ሞላ፥ ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉ ታላላቅ ሁነቶችን የማስተናገድ በቂ ልምድ ያላት በመሆኑ፣ ኮንፈረንሱን በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ አስፈላጊው ዝግጅት እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
#EBC #EBCDOTSTREAM #WIC #InternetConference #Ethiopia #Technology #Innovation #AddisAbaba