Search

ኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም በልማት አጋርነት ላይ በቅርበት አብሮ ለመሥራት ተስማሙ

እሑድ ጥር 17, 2018 241

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ከዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ፕሬዚዳንት ሚስተር ቦርጌ ብሬንዴ ጋር ተገናኝቶ ተወያይቷል።

ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ስላለው ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሂደት ማብራሪያ ሰጥተዋል፤ አጋርነትን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ አጋሮች ጋር ወቅታዊ በሆኑ የዓለም አቀፍ ልማት፣ የቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ እንድትወያይ ይህንን ጠቃሚ መድረክ በማመቻቸቱ ለዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱም ወገኖች በኢንቨስትመንት ውይይት እና በልማት አጋርነት ላይ በቅርበት አብሮ ለመሥራት ተስማምተዋል።

የኢትዮጵያ ልዑክ የሀገራችንን ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች በማስጠበቅ እና ለዘላቂ ልማት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጋር በጋራ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት በማሳየት፣ ኢንቨስትመንትን እና አጋርነትን ለማሰባሰብ ያለሙ ስኬታማ ተግባራትን በማከናወን በዳቮስ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም 2026 ላይ የነበረውን ተሳትፎ አጠናቅቋል።

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #WEF2026 #Davos2026 #finance