Search

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ6 ወራት ውስጥ ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገበ

እሑድ ጥር 17, 2018 251

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል።

ባንኩ በያዝነው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት 124.12 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን በትናንትናው ዕለት በተጠናቀቀው የግመሽ ዓመት ጉባኤው ላይ ተገልጿል።

ገቢው የስድስት ወሩ ዕቅድ አፈጻጸም 107% ያሳካ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ56% ብልጫ እንዳለውም ተነግሯል።

በሀገር ደረጃ እየተተገበረ ያለው የኢኮኖሚክ ሪፎርም እና እሱን ተከትሎ የፋይናንስ ምኅዳሩ በቁጥርም ሆነ በመጠን ማደጉ፣ ከአዳዲስ የአሠራር ደንቦች እና ታሪፎች መተግበር ጋር ተዳምሮ ለተገኘው አጠቃላይ ገቢ መጨመር የጎላ አስተዋፅኦ አድርጓል ተብሏል። 

በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመንፈቅ ዓመቱ ያልተጣራ የ36.19 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን በጉባኤው ተገልጿል።

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #CBE #Profit #successstory 📈