በጅማ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የሚካሄደው 10ኛው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ውድድር ፌስቲቫል ዛሬ በድምቀት ተከፍቷል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ስፖርትን ከመዝናኛነት ባለፈ የህዝቦች አብሮነትና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተጀመረው በዚህ ታላቅ ስፖርታዊ መድረክ ላይ፦
📌 ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይሳተፋሉ።
📌 በ15 የስፖርት ዓይነቶች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ውድድሮች ይካሄዳሉ።
ውድድሩ የተማሪዎችን ስፖርታዊ ተሰጥዖ ለመለየት፣ ባህላዊ እሴቶችን ለመለዋወጥ እና የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
እንዲህ ያሉ መድረኮችን ለማስፋፋት መንግሥት የስፖርት ማዘውተሪያ መሠረተ ልማቶችን በስፋት እየገነባ መሆኑንም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
#EBCDotstream #Ethiopia #Universities #SportsFestival #JimmaUniversity #Unity #Fraternity