Search

በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የአቪዬሽን አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ውይይት ተደረገ

ረቡዕ ጥር 20, 2018 178

የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት ጉብኝት አደረጉ።
የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ከአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና ከተቋሙ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ጋር የሥራ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በዋናነት በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር፣ የአቪዬሽን ዘርፍ ልማትን ማሳደግ እንዲሁም በወደፊት የሥራ ዕድሎች ዙሪያ ላይ ያተኮረ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።
የአየር መንገዱ የሥራ አመራሮች የአሜሪካ የልዑካን ቡድንን በአየር መንገዱ ዋና መሥሪያ ቤት ተቀብለው በማወያየታቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለፁ ሲሆን፣ ይህ ግንኙነት በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የአቪዬሽን አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው አየር መንገዱ አስታውቋል።
 
በአፎሚያ ክበበው