የሐረሪ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ አልሚዎች በክልሉ እንዲያለሙ የመሥሪያ ቦታ በምደባ እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል።
የመሥሪያ ቦታ እንዲሰጥ ውሳኔ የተላለፈውም ልዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው በተለይ በሆቴል እና ቱሪዝም፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ እና ማኑፋክቸሪንግ፣ በቅይጥ አገልግሎት እና በጋራ የመኖሪያ ቤት አፓርትመንት እንዲሁም በመዝናኛ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ነው።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በአጀንዳው ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
የክልሉ መንግሥት የኢንቨስትመንት ዘርፉን የበለጠ ለማነቃቃት በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተመላክቷል።
በቀጣይም ፋይዳ ባላቸው እና የሕዝብን ተጠቃሚነት በሚያጎለብቱ ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
#EBC #EBCDotstream #Ethiopia #Harari