በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተኪ ምርትን ሳይጨምር በኢንዱስትሪው ዘርፍ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኤክስፖርት እንደምታደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ መሆኑን ገልጸው፤ የኢንዱስትሪዎች የኤክስፖርት ምጣኔ በእጥፍ ማደጉን አመላክተዋል።

ከሦስት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ሲጀመር በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ኢንዱስትሪዎች ማምረት የሚችሉት ከ47 እስከ 48 በመቶ ድረስ ነበር፤ ዛሬ ላይ ኢንዱስትሪዎቹ 66 ነጥብ 3 በመቶ የማምረት ምጣኔ ላይ ደርሰዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አጠቃላይ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ቢዝነሶች ውስጥ 413 ሺህ የሚሆኑት አምራች ኢንዱስትሪዎች መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
ከውጪ ይገቡ የነበሩ ምርቶችንም በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተሰራው ሥራ ከውጭ ይገባ የነበረ የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ምርት በሀገር ውስጥ መተካቱንም ገልጸዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ
ኢቢሲ ዶትስትሪም - የመረጃዎ ድልድይ! ሙሉውን ዘገባ እና ዝርዝር መረጃዎችን በኢቢሲ ዶትስትሪም ዲጂታል አማራጮች ይከታተሉ።