Search

በምንም መልኩ ለሳይበር ማጭበርበር ልንጋለጥ እንችላለን?

 
አብዛኛዎቻችን በተለያዩ አጋጣሚዎች በማሕበራዊ ሚዲያ፣ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ፣ በስልክ ወይም ከማናዉቀዉ አካል መልዕክት ወይም የስልክ ጥሪ አስተናግደናል።
እነዚህ መልዕክቶችና የስልክ ጥሪዎች በአብዛኛዉ አሳማኝ፣ በጣም አጓጊና ቀልብ የሚስቡ በመሆናቸዉ ሳንጠራጠር ያሉንን እናደርጋለን።
በዚህም በአጭበርባሪዎች እጅ እንወድቃለን።
ለመሆኑ አጭበርባሪዎች የሚፈልጉትን ነገር ከኛ ለማግኘት የትኞቹን ማጭበርበሪያ ስልቶች ይጠቀማሉ፡-
👉በተለይ በማሕበራዊ ሚዲያ በመተዋወቅና የፍቅር ጓደኝነት በመጀመር የጥቃት ኢላማ የሆነን አካል በፍቅር ስም ማጭበርበር፤
👉ትርፍ_ለማግኘት_ባለን_ፍላጎት ላይ በመነሳት ብዙ ገንዘብ የምናገኝበት አማራጭ እንዳላቸዉ በማስመሰል የሚፈጸም ማጭበርበር፤
👉አጭበርባሪዎች በበይነ መረብ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን የሚገዙ ወይም የሚሸጡ በመምሰል የሚፈጽሙት ማጭበርበር፤
👉አጭበርባሪዎች ግላዊ መረጃዎቻችንን በመጥለፍና እንደጠለፉ በማስመሰል እንዲሁም መረጃዉን ይፋ እንደሚያደርጉ በማስፈራራት ያጭበረብራሉ፤
👉ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ሥራ እንደሚያስቀጥሩን በማግባባት ለቅጥሩ ቅድመ ክፍያ በመጠየቅ የሚፈጸም ማጭበርበር፤
👉ያልቆረጥነዉን ሎተሪ ወይም ያልተሳተፍንበትን ውድድር እንዳሸነፍን በማሳመን የሚፈጸም ማጭበርበር፤
👉አጭበርባሪዎች እምነት የሚጣልበት ተቋም፣ የቅርብ ወዳጅ ወይም ቤተሰብ መስሎ በመቅረብ የሚፈጸሙ ማጭበርበሮች፤