Search

🔍ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት የሚረዱ ስልቶች

🔍ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት የሚረዱ ስልቶች
📍 1. የመረጃውን ምንጭ መለየት (consider the source)
የአንድን ይዘት ምንጭ በማጣራት ስለይዘቱ ትክክለኛነት ወይም ሀስተኝነት እና ተያያዥ ነገሮች ማወቅ ይቻላል። በመሆኑም ይዘቱ ፖስት የተደረገበትን ድረ-ገጽ፣ አላማውን እና አድራሻውን በትኩረት መመልከት ስለይዘቱ ግንዛቤ እንዲኖረን ያግዛል።
📍 2. ከርዕሱ አልፎ ማንበብ (Read beyond the headline)
ይዘቶችን እንዲነበቡ ወይም እንዲታዩና እንዲደመጡ ለማድረግ ርዕሶች ወጣ ባለ መልኩ ሊጻፉ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜም ይዘቱ እና ርዕሱ ስለማይገናኝ ከርዕሱ ባሻገር ያለውን ነገር ጠለቅ ብሎ ማንበብ ያስፈልጋል።
📍 3. መረጃውን ያወጣውን ግለሰብ መለየት (Check the author)
ይዘቱን ያዘጋጀውን ግለሰብ ማንነት በይዘቱ ላይ ስለሚኖረን አተያይ ፍንጭ የሚሰጥ ይሆናል። አዘጋጁ ተዓማኒነት ባለው ዓላማ እና እውቀት ላይ ይመሰረታል። አዘጋጁስ እውነተኛ ሰው ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስም ተገቢ ይሆናል።
📍 4. አጋዥ ምንጮችን ማየት / supporting sources/
ለዋናው ይዘት እንደማስረጃ የቀረቡት ዝርዝር ሃሳቦች ምን ያክል አስረጅና ደጋፊ ናቸው? የሚለውን በተለያየ አቅጣጫ መመልከት እና ማረጋገጥ ተገቢ ነው።
📍 5. የተጫነበትን ቀን እና ሰአት ማስተዋል (check the time & date)
አንዳንድ ጊዜ የቆዩ መረጃዎችን አዲስ በማስመሰል ፖስት የማድረግ ሁኔታዎች ስላሉ ቀኖችን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
📍 6. ቀልድ /ቧልት/ መሆንና አለመሆኑን ማረጋገጥ / check if it is a joke /
የመረጃዎችን እውነተኛነት ወይም ቁምነገርነት ለማረጋገጥ የይዘቱን ምንጭና ሌሎች ጉዳዮችን መመልከት ይቻላል። አንዳንድ መረጃዎች ሳቅ ለመፍጠር መበማለም ብቻ ሀሰተኛ መረጃዎች ፖስት ስሚደረጉ እሱን ማረጋገጥ ተገቢ ይሆናል።
📍 7. የእኛን ገለልተኝነት ማረጋገጥ /check your bias/
በተለያየ ምክንያት የራሳችንን ወገንተኝነት ማጤን በጉዳዩ ላይ ከሚኖረን አድልዎ ነጻ ሆነን የተለያዩ ይዘቶችን ለመረዳትና ለመመርመር መሞከር ተገቢ ነው። ምክንያቱም ይዘነው የመጣነው አስተሳሰብ በይዘቶች ላይ በሚኖረን አረዳድ ላይ ተጽዕኖ ይፈጥሬል።
📍 8. የዘርፉ ባለሙያዎችን መጠየቅ /ask experts/
ሀሰተኛ መረጃዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ተከትሎ መረጃ ማጣራት ላይ የሚሰሩ ተቋማትን አልያም በጉዳዩ ላይ ባለሙያ የሆኑ አልያም በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለሙያዎችን /ተቋማትን/ መጠየቅ መፍትሄ ይሆናል።
 
ለተጨማሪ መረጃዎች የኢቢሲ ፋክት ቼክ የፌስቡክ ገፅን ይጎብኙ 
https://web.facebook.com/profile.php?id=61550945701729