Search

የኢቢሲ ዜና ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ የትኛው ነው?

Aug 09, 2025

ሀሰተኛ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ተመሳስለው በሚከፈቱ ገፆች (አካውንቶች) በስፋት ሲሰራጩ ይስተዋላል።
እነዚህ ሀሰተኛ ገፆች በከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ማህበራዊ አንቂዎች፣ በግል፣ የመንግስት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም በሚድያዎች ስም ተመሳስለው የሚከፈቱ ናቸው።
ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆች ተመሳሳይ ስም፣ ተመሳሳይ የፕሮፋይል ፎቶግራፎች እና ተመሳስለው የተቀረፁ መልእክቶችን ይዘው የሚከፈቱ በመሆናቸው ከትክክለኛዎቹ ማህበራዊ ገፆች ጋር ለመለየት አስቸጋሪ ይሆናሉ።
ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የኢቢሲ ዶትስትሪም ማህበራዊ ገፆችን ጨምሮ አብዛኞቹ ታዋቂ ገፆች የትክክለኛነት ማረጋገጫ ምልክት (verification badge) ያገኙ በመሆናቸው ለትክክለኝነታቸው ቀላሉ እና የመጀመሪያው ማረጋገጫ ከገፆቹ ስም አጠገብ የሚቀመጠው ሰማያዊ ምልክት ነው።
ኢቢሲ ፋክት ቼክ በዚህ መልኩ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለማጋለጥ ትክክለኛ ገፆችን በመለየት ለተከታዮቹ ተከታታይ መረጃዎችን ያቀርባል።
ከ4 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው፣ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ምልክት (verification badge) ያገኘ ነው የኢቢሲ ዜና የፌስቡክ ገፅ።
የኢቢሲ ዶትስትሪምን ትክክለኛ የፌስቡክ የኤክስ፣ የዩቲዩብ፣ የቲክቶክ እና የኢንስታግራም፣ ዌብሳይት እና ቴሌግራም ገፆችን ከስር በተቀመጡት ማስፈንጠሪያዎች ማግኘት ይችላሉ።
በምስሉ ላይ የተጠቀምናቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገፆች በመሆናቸው በስህተት ከመከተል እንድትጠነቀቁ ለማስገንዘብ ተለይተው የተቀመጡ ናቸው።
ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የማህበራዊ ገፆች