ሀቅን/ እውነታን በማጣራት ሂደት ውስጥ ተያያዥ ግን የተለያዩ 5 ደረጃዎች ያሉ ሱሆን እነሱም እንደሚከተለው ቀርበዋል::

በማህበራዊ ሚድያ ላይ በታዋቂ ሰዎችና በሚዲያ ተቋማት የተነገሩ እና የተባሉ ነገሮችን መፈተሽ፣ የምንጮችን ተዓማኒነት መጠየቅና የማጣራት ስራዎችን የምንሰራበት የመጀመሪያው ሂደት ነው፡፡

ያለውን ማስረጃ መለየትና በመረጃው ዙሪያ ያለውን ዳራ መረዳት፡፡ ይህም የመጨረሻውን ድምዳሜ ለመወሳን ወሳኝ ሚና ይኖረዋል::
3 መረጃን ማመሳከር፡-
በዚህ ሂደት የመረጃውን ምንጭ፣ እድሜውን፣ ዳራውን መሰረት በማድረግ የመረጃውን ተዓማኒነት መመዘን

ግኝቶችን የሚያረጋግጡ ሌሎች ምንጮን ማስባሰብ ስራ የምንሰራበት ሂደት ነው:: የሚኖሩትን ልዩነቶችና መጣራሶችም ጭምር የምናብራራበት ሂደት ነው፡፡

በማጣቀስ የተገለጡ ነገሮችንና መረጃዎችን በሙሉ ምንጫቸውን መግለጽ:: ይህም ስሙ የተጠቀሰው ሁሉ መልስ እንዲሰጥ እድሉን ይሰጣል:: ይህ አሰራር መረጃ የማጣራት ሂደትን የሚገልጽ ሲሆን የስራ ክፍፍልን እና ሃላፊነትን በተመለከተ የሚዲያ ተቋማቱ ባላቸው የሰው ሃይል እና የመስሪያ ቁሳቁስ ተመስርተው መዋቅራቸውን ሊዘረጉ ይችላሉ::
ለሁሉም ድርጅቶች የሚሰራ ወጥ የሆነ መዋቅር መዘርጋት አስቸጋሪ ስለሚሆን እያንዳንዱ ተቋም ባለው ባለሙያ እና ሌሎች ግብዓቶች ላይ ተመስርቶ የአሰራር መዋቅሩን መዘርጋት ይችላል።