በሀምሌ ወር መገባደጃ ላይ በሩሲያ ካምቻትካ ባሕረ ገብ መሬት ላይ በደረሰ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ጃፓንን ጨምሮ በፓስፊክ ውቅያኖስ አካባቢ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ይታወሳል።
ታድያ ይህን ክስተት ተከትሎ በቲክ ቶክ እና በፌስ ቡክ የተጋራ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ከ39 ሚሊዮን በላይ ዕይታን በማግኘት በፍጥነት በመሰራጨት የተሳሳተ መረጃ ሲያደርስ ቆይቷል።
ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከአውሮፕላን ላይ የተቀረፀ የሚመስል ሲሆን ጃፓን በከባድ ሱናሚ ስትመታ ያሳያል።
ነገር ግን ይህ ሐሰተኛ ምስል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ መሆኑን ኤ.ኤፍ.ፒ ፋክት ቼክ አረጋግጧል።
ተንቀሳቃሽ ምስሉ በመጀመሪያ በዩቲዩብ ቻናል ላይ የተጋራ ሲሆን የቻናሉ ባለቤት ሰውሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የተሰሩ ምስሎችን ብቻ እንደሚያጋራ በግልፅ በቻናሉ የፊት ገፅ ላይ አስቀምጧል ሲል ገልጿል።
#ebcdotstream #etv #EBC #FactCheck #fakenews #Scams #cybersecurity