Search

የ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከበረ

ዓርብ መጋቢት 11, 2018 27

1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ተከብሮ ውሏል።

በመዲናዋ አዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 28 "የተስፋ ብርሃን" የምገባ ማዕከላት ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ያጋሩ ሲሆን፣ በመዲናዋ የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ባህል በከፍተኛ ሁኔታ እየዳበረ መሆኑን ገልጸዋል።

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማም በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት የተከበረ ሲሆን፣ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ያሲን ከሊል በረመዳን የታዩ የመረዳዳት እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይ በሐረር፣ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ በጅማ፣ በሐዋሳ፣ በአርባ ምንጭ፣ በአሶሳ፣ በወላይታ ሶዶ በሰቲት ሁመራ እና ሌሎች ከተሞች በዓሉ በታላቅ የዒድ ሶላት እና በሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ተከብሯል።

በየከተሞቹ በተላለፉ መልዕክቶችም በዓሉን የተቸገሩትን በመርዳት፣ ሰላምን በማጠናከር እና አብሮነትን በማጎልበት ማክበር እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶታል።

በተለይም በአርባ ምንጭ ከተማ ለመሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጂዎች የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ መከናወኑ እና በወራቤ የተለያዩ ተቋማት ያሳዩት ማህበራዊ ኃላፊነት የበዓሉ ልዩ ገጽታዎች ነበሩ። በአጠቃላይ በዓሉ በመላ ሀገሪቱ በሰላም እና በአንድነት ተከብሮ መጠናቀቁ ተመልክቷል።