የዘንድሮውን የምርጫ ሂደት ይበልጥ አካታች፣ ዘመናዊና ተዓማኒ ለማድረግ የቴክኖሎጂ ትግበራና አካታች አሰራርን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።
ይህ የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች አባላት የሚመረጡበት ይፋዊ ሂደት ከምርጫ ቁጥር ባሻገር የዜጎችን የነቃ የፖለቲካ ተሳትፎና የሀገራዊ አንድነት ጽኑ እምነት ያሳየም ሆኗል።
የዘንድሮው ምርጫ ካለፉት የምርጫ ታሪኮች የተገኙ ድክመትና ጥንካሬዎችን መነሻ በማድረግ፣ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ገለልተኝነት ለማሳደግና በሂደቱ ላይ የዜጎችን እምነት ለመገንባት አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ይዞ መጥቷል።
ይህ ታሪካዊ የምርጫ ድምፅ የሕዝብ ሕሊና፣ የሀገር ተስፋ እና የትውልድ አደራ መግለጫ በመሆኑ፣ የምርጫው ሂደት በሰላም ተጠናቆ ሀገራዊ ስኬት እንዲመዘገብ ዜጎች በቁርጠኝነትና በሀገራዊ ፍቅር በካርዳቸው እንዲመርጡ ጥሪ ቀርቧል።
በበረከት ሽመልስ