Search

ብልፅግና ፓርቲ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና የፓርቲውን የምርጫ ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀመረ

ቅዳሜ ግንቦት 29, 2018 8

የብልፅግና ፓርቲ የጠቅላላ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲሁም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲውን የዕቅድ አፈጻጸም በጅግጅጋ ከተማ መገምገም ጀመረ።

ፓርቲው በምርጫ ዕቅዱ መሠረት በቅድመ ምርጫ እና በምርጫው ወቅት የነበረውን አጠቃላይ አፈጻጸም በጥልቀት እየገመገመ ነው።

በመድረኩ ላይ በሂደቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ ለማሳደግና በድክመት የተለዩ አፈጻጸሞችን በማረም ረገድ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።