Search

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ የወጪ ንግድ ገቢን እያሳደገ ያለው የኢትዮጵያ የግብርና ኢንቨስትመንት

ሰኞ ሰኔ 01, 2018 99

ኢትዮጵያ በአስር ዓመቱ የግብርና መሪ ዕቅድ ውስጥ በትኩረት እንዲሰራባቸው ካስቀመጠቻቸው ስትራቴጂካዊ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው የግብርና ኢንቨስትመንት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት እና የውጪ ምንዛሪን የማሳደግ ሀገራዊ ግቦችን በላቀ ስኬት እያሳካ ይገኛል።

የሀገራችንን ሰፊ የግብርና አቅም በመጠቀም በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በስፋት ተሰማርተው ወደ ልማት ገብተዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ በእርሻ ኢንቨስትመንት ብቻ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት 8 ሺህ 904 ባለሀብቶች እጅ ላይ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

መንግሥት ይህንን ዘርፍ ይበልጥ ለማሳደግ በመሬት አቅርቦት፣ የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ፣ በውል እርሻ እና በመሰረተ-ልማት ማመቻቸት ረገድ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪም የግብርናውን ዘርፍ ሽግግር የሚያፋጥኑ የሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለባለሀብቶች የማስተዋወቅ ስራ በትኩረት እየተከናወነ ሲሆን ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተተገበሩ ዘመናዊ አሰራሮች፣ በኮንትራት እርሻ፣ በምርጥ ዘር ብዜት እንዲሁም በአካታች የሕግ ማዕቀፎች ምክንያት አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።

በአሁኑ ወቅት አበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሰብል እና እንስሳት በኢንቨስትመንት ደረጃ በስፋት እየለሙ ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለወጪ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ እየቀረቡ ይገኛሉ።

ለአብነትም የአበባ፣ የአትክልት እና የፍራፍሬ የወጪ ንግድ አፈፃፀምን ስንመለከት 2013 . 309 ሺህ 866 ነጥብ 8 ቶን ምርት 531 ሺህ 480 ዶላር ተገኝቷል።

ይህ ቁጥር 2017 . እጅግ ከፍተኛ ዕድገት በማሳየት ከተላከው 395 ሺህ 911 ነጥብ 9 ቶን ምርት 670 ሺህ 627 ነጥብ 4 ዶላር ገቢ ለማግኘት ተችሏል።

የዘንድሮውን 10 ወራት አፈፃፀም ስንመለከት ደግሞ 236 ሺህ 415 ነጥብ 3 ቶን ምርት 408 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያረጋግጣል።

በሌላ በኩል ለሀገራዊ ኢኮኖሚ፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለእውቀት ሽግግር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው የእንስሳት ኢንቨስትመንትም ሌላው ትኩረት የተሰጠው ዘርፍ ነው።