ከሶስት ቀናት በኋላ በሚጀምረው የ2026ቱ ዓለም ዋንጫ፣ ፊፋ በታሪክ ከፍተኛ የተባለውን የ14 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህም በ2022 በኳታር ከተካሄደው የዓለም ዋንጫ ከተገኘው ገቢ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን፤ አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ የሚያዘጋጁት ይህ ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት ሀገራት አስተናጋጅነት የሚካሄድ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ በመሆን አዲስ ታሪክ ይጽፋል።
ይህ በዓይነቱ ትልቁ የተባለው የዘንድሮው ዓለም ዋንጫ የተሳታፊ ሀገራትን ቁጥር ወደ 48 ያሳደገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 104 ጨዋታዎች ይደረጉበታል።
ይህ የተሳትፎ መጠን ውድድሩን በታሪክ ትልቁ ከማድረጉም በላይ፣ በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛ ትርፍ የሚመዘገብበትና በገንዘብ ረገድ እጅግ ስኬታማው የስፖርት ሁነት እንደሚያደርገው ታውቋል።
በዘረንቶስ ሰለሞን