Search

የገዳ ሥርዓት የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት መብት ያረጋገጠ ሥርዓት ነው - የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን

ሓሙስ ሰኔ 04, 2018 56

71ኛው የቱለማ ገዳ ሥርዓት የአለንጌ (ሥልጣን) ርክክብን ምክንያት በማድረግ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የገዳ ሥርዓት የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት መብት ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

ሥርዓቱ የሕዝብን በራስ የማስተዳደር መብት በማረጋገጥ እና የፖለቲካ ሥልጣንን በመምራት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል።

ያለምንም ራስ ወዳድነት እና ግጭት ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ የሚሸጋገርበት የገዳ ሥርዓት ገዳ የኦሮሞ ሕዝብ ለሀገር እና ለዓለም ያበረከተው ነው ብለዋል።

የቱለማ ገዳ እያደገ እና እየበለጸገ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመው፣ አባቶች ተንከባክበው እና ጠብቀው እዚህ ያደረሱትን የገዳ ሥርዓት አዲሱ ትውልድ እሴት በመጨመር ለታሪክ እንዲያስቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የቱላማ ገዳ ሥልጣን ሽግግር ሥነ ሥርዓት የገዳ ከሰኔ 4 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ሁነቶች የሚካሄድ ሲሆን፣ ሥልጣን ከገዳ ሜልባ ወደ ገዳ ሙደና የሚሸጋገርበት ሆኑን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።