23ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ በይፋ ሲጀመር ሜክሲኮን የገጠመችው ደቡብ አፍሪካ 2 ለ 0 ተረታለች።
የሜክሲኮን የማሸነፊያ ግቦች ዩሊያን ኩዊኖኔስ በመጀመሪያው አጋማሽ 9ኛው ደቂቃ ላይ እንዲሁም፤ ራውል ሂሚኔዝ 68ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል።
በሁለተኛው አጋማሽ 50ኛው ደቂቃ ላይ የደቡብ አፍሪካው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ስፊፎሌ ሲቶሌ ብሪያን ጉቴሬዝ ላይ በፈፀመው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
በዚሁ ጨዋታ ሁለተኛውን ቀይ ካርድ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሰባት ደቂቃዎች እየቀሩ ቴምባ ዝዋን ተመልክቷል። ይህ በ'ባፋና ባፋና' የመድረኩ ተሳትፎ ታሪክ አራተኛ ቀይ ካርድ ሆኖ ተመዝግቧል።
በጭማሪው ሰዓት 92ኛው ደቂቃ ላይ የሜክሲኮው ሴዛር ሞንቴዝ የጨዋታውን ሦስተኛ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።
የ23ኛው ዓለም ዋንጫ መክፈቻ፣ የታሪካዊው አዝቴክ ስታዲየም 21ኛ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ፣ የሀገራቱ 2ኛ የእርስ በእርስ ግንኙነት በ'ትሪ ከለርስ' አሸናፊነት ተጠናቋል።
ከዓለም ዋንጫው አስተናጋጆች አንዷ ሜክሲኮም ምድብ አንድን ከወዲሁ መምራት ጀምራለች።
የምድብ አንድ ሌላኛው ጨዋታ በነገው ዕለት በደቡብ ኮሪያና ቼክ ሪፐብሊክ መካከል ይደረጋል።