የሊቨርፑሉ አጥቂ ሙሀመድ ሳላ በእግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
ግብጻዊው አጥቂ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ለ20ኛ ጊዜ ሲያነሳ ትልቁን ሃላፊነት ተወጥቷል።
በግሉም ምርጥ የውድድር ዓመት ያሳለፈው ሳላ በሊጉ 29 ግቦችን ሲያስቆጥር 18 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል።
ለ52ኛ ጊዜ በተደረገው ሽልማት ደክለረን ራይስ፣ ቡሩኖ ፈርናዴዝ፣ አሌክሳንደር ይሳቅ፣ አሌክሲስ ማክ አሊስተር እና ኮል ፓልመር የመጨረሻ ዕጩዎች ሆነው የቀረቡ ተፎካካሪዎቹም ነበሩ።
የማንችስተር ሲቲው አማካይ ፊል ፎደን የባለፈው ዓመት አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል።
የእንግሊዝ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር ሽልማት በ50 ዓመታት ጉዞው ማንችስተር ዩናይትድ 11 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚው ክለብ ነው።
በአንተነህ ሲሳይ