Search

በሴኔጋል ዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል ተደረገ

ቅዳሜ ኅዳር 05, 2019 193

በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በሴኔጋል መዲና ዳካር በተካሄደው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የፌዴሬሽኖች አመራሮች በተገኙበት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሴኔጋል መዲና ዳካር በተካሄደው በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ ልዑክ አምስት ወርቅ እና ሶስት የብር በጥቅሉ ስምንት ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ፣ በአትሌቲክስ ውድድሮች ከቻይና፣ ኬኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ ቀድሞ ሰንጠረዡን በበላይነት ማጠናቀቁ ይታወሳል።

በዘረንቶስ ሰለሞን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: