በትግራይ ክልል ባለ አደራ አስተዳደር የመጠጥ ውኃ እና ሳኒቴሽን አቅርቦት ዳይሬክቶሬት፣ ከመላው ሠራተኞቹ ጋር በመመካከር የቀጣዮቹን ስድስት ወራት የሥራ ዕቅድ በጋራ መግባባት ማጽደቁን አስታወቀ።
በዕቅዱ መሠረት የከተሞችን የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ሽፋን ወደ 40 በመቶ፣ የገጠሩን ደግሞ ወደ 45 በመቶ ለማድረስ ተይዟል።
የማይሠሩ የውኃ ተቋማትን መጠን ወደ 25 በመቶ ዝቅ ማድረግ እና የከተሞችን የውኃ ብክነት ወደ 20 በመቶ ማውረድም ትኩረት ተሰጥቶታል።
በድርቅ ወቅት የሚከሰተውን የውኃ እጥረት ለማቃለል ፈጣን እና ዘላቂ መፍትሔዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ።
ግቦቹን በስኬት ለማሳካትም ከፌዴራል መንግሥት እንዲሁም ከመንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ አጋር ተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር ለመሥራት ጥሪ ቀርቧል።
በአስማረ ብርሃኑ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: