Search

አንድ አሽከርካሪ የግጭት ጉዳት የደረሰበትን ተሽከርካሪውን ወደ ጋራዥ ከመውሰዱ በፊት ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?

ቅዳሜ ጥቅምት 29, 2018 334

አንድ አሽከርካሪ በትራፊክ አደጋ የተነሳ ጉዳት የደረሰበትን ተሽከርካሪውን ለጥገና ወደ ጋራዥ ከመውሰዱ በፊት የአደጋውን ሁኔታ የሚተነትን ማስረጃ ከፖሊስ መያዝ እንደሚገባው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ገልጿል።

በባለስልጣኑ የትራፊክ ቁጥጥር እና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አያሌው አብዲሳ ለኢቢሲ ዶትስትሪም እንደገለጹት፥ አንዳንድ አሽከርካሪዎች በተሽከርካሪ ላይ የግጭት ጉዳት ካደረሱ በኋላ ከሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ተሽከርካሪውን በፍጥነት ወደ ጋራዥ በመውሰድ ይዘቱን ያስቀይራሉ።

ይሁን እንጂ በመንገድ ትራንስፖርት የትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016 መሠረት፥ አሽከርካሪው የግጭት ጉዳት የደረሰበትን ተሽከርካሪውን ወደ ጋራዥ ወስዶ ከማስጠገኑ በፊት የግጭቱን ወይም የአደጋውን ሁኔታ የሚመለከት ማስረጃ ከፖሊስ መያዝ ይጠበቅበታል ብለዋል።

ይህን ማስረጃ ሳይዝ የተጎዳውን ተሽከርካሪ ወደ ጋራዥ ወስዶ ቢያስጠግን የጥገና አገልግሎቱን የሰጠው ጋራዥ በወንጀል ከመጠየቁ በተጨማሪ እስከ 20 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ ገልጸዋል።

በሔለን ተስፋዬ

#ebcdotstream #TMA #traffic #vehiclecollision #regulation