Search

ጊዜ ያለፈባቸው አሰራሮችን እየቀየርን ኢትዮጵያን ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ እየሰራን ነው፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ሓሙስ መጋቢት 17, 2018 112

በኢትዮጵያ ጊዜ ያለፈባቸው አሰራሮችን በማዘመን ሀገራችንን ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡
"4ኛው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ" ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረምን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጀምረዋል።
ፎረሙ አጋርነትን ለማጠናከር እና የጋራ ብልጽግና የሚፈጥር መጻኢ ዕድልን ለመቅረጽ ያለመ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራዕይን ከተግባር፣ ምኞትን ደግሞ ከኢንቨስትመንት ጋር የሚያገናኝ መድረክ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ስር ጥልቅ እና ወሳኝ ሪፎርሞችን ማከናወኗ የግል ዘርፉን ተሳትፎ እያሰፋ እና በኢኮኖሚው ውስጥ የንግድ ድርጅቶችን ሚና እየቀየረ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ሪፎርሞቹ መሰረታቸውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ መሆናቸውን ያሳወቁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአጋሮቻችንን ፍላጎት እያከበርን የሕዝባችንን ፍላጎትና ምኞት በተሻለ ሁኔታ የሚመልሱ ስራዎችን እንሰራለን ነው ብለዋል።
በተለይም ወጣት፣ ንቁ እና ብቁ የሆነው ሕዝባችን ተጠቃሚነትን የሚጨምሩ አስቻይ ሁኔታን ለመፍጠር በትኩረት አንደሚሰራም አረጋግጠውል።
"በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ"ፎረም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ የሚከናወኑ ጥረቶች አንዱ አካል ነው፡፡
ባለፈው ዓመት በተካሄደው "በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ" ፎረም ከአምስት ግዙፍ ኩባንያዎች ጋር ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመቱ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች የተፈረሙ ሲሆን ስምምነት የፈረሙ ሁሉም ኩባንያዎች በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡
በዘንድሮው ፎረም ደግሞ ከዚህ የላቁ ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአሸናፊ እንዳለ