በከተማዋ በኮሪደር ልማት የተሠሩ የሳይክል መንገዶች በተለያዩ የዕድሜ ክልል ለሚገኙ የሳይክል ተጠቃሚዎች ተመራጭ ሆነዋል።
ይህ በጎ ሥራ ከተጠቃሚዎቹ ባሻገር ለሳይክል ሻጮችም ገቢ ሰፊ መነቃቃትን ፈጥሯል።
የሳይክል ትራንስፖርት ከስፖርታዊ እና ተዝናኖታዊ አገልግሎት ባሻገር የመዲናችን አማራጭ ትራንስፖርት በመሆን ላይ መሆኑን በርካቶች ይገልጻሉ።
ለዚህም በከተማው ከዋና መንገዶች ዳር ከእግረኞች መንገድ ጋር ተሰናስሎ የተሠራው የኮሪደር ልማት መንገድ ብዙዎች ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ እና ለመዝናናት ተመራጭ አርገውታል።
ወጣት ባህሩ ከኬሎች ጓደኞቹ ጋር በማኀበር ተደራጅተው በሳይክል ንግድ ሥራ ላይ መሳተፍ ከጀመሩ በርካታ ዓመት እንደሆናቸው ተናግሯል።
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የሆነው ወጣቱ ከ2 ዓመት ጀምሮ ለሆኑ ሕፃናት እና ለአዋቂዎችም የሚሆኑ ሳይክሎችን እንደሚያቀርቡ ተናግሮ፤ የህፃናት ሳይክል በአማካይ ከ 13 ሺህ ብር ጀምሮ እንደሚሸጥ ገልጿል።
ሳይክል ለመገበያየት የሚመጡ ደንበኞቻችን እንደየፍላጎታቸው የኤሌክትሪክ ሳይክልን ጨምሮ በተለያዩ ዋጋዎች የሚያገኙ ሲሆን ብዙዎች ለኮሪደር ልማቱ የኤሌክትሪክ ሳይክልን ይመርጣሉ ብሏል።
የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ጥራታቸውን የጠበቁ የአዋቂ ሳይክሎች ከ29ሺህ ብር ጀምሮ እስከ 50 ሺህ ብር እየተሸጡ እንደሆነ እና የውድድር ሳይክሎች ደግሞ ከ200 ሺህ ጀምሮ እስከ 400 ሺህ እንደሚሸጡ ጠቅሷል።
ባጠቃላይ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ባህሩ የሳይክል ሽያጩ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በፈጠረው መነቃቃት ማህበረሰቡ እየተገበያየ እንደሆነ ተናግሯል።
በሄለን ተስፋዬ
አዳዲስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የኢቢሲን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር እና ፕለይ ስቶር አውርደው ዲጂታል ኢቢሲን ይቀላቀሉ።
አንድሮይድ (Android) ስልክ የምትጠቀሙ በዚህ ሊንክ
https://shorturl.at/6KegY
አይኦኤስ (iOS) ስልክ የምትጠቀሙ ደግሞ በዚህ ሊንክ
https://shorturl.at/hFuA1