የእንግሊዝ ታላለቅ ክለቦች በንቃት የተሳተፉበት የ2025 የክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሊዘጋ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡
ሊቨርፑል በርካታ ገንዘብ በማውጣት በቀዳሚነት ሲቀመጥ ፉልሀም ዝቅተኛውን ወጭ አድርጓል፡፡
ከ20 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች 12ቱ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ወጭ አድርገዋል፡፡
ሊቨርፑል የክለቡ ክብረ ወሰን በሆነ ገንዘብ ከባየር ሊቨርኩስን ያስፈረመውን ፍሎሪያን ቨርዝን ጨምሮ በአጠቃላይ እስከ አሁን 291.9 ሚሊዮን ፓውንድ ወጭ በማድረግ ቀዳሚው ሆኗል፡፡
ሰባት ተጫዋቾችን ያስፈረመው አርሰናል 252.6 ሚሊዮን ፓውንድ በማውጣት 2ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡ ቼልሲ 240.1 ሚሊዮን ፓውንድ ሲያወጣ ፡ ማንችስተር ዩናትድ 197.2 እና ማንችስተር ሲቲ 153.4 ሚሊዮን ፓውንድ በማውጣት ከ3ኛ እስከ 5ኛ ተቀምጠዋል፡፡
ፉልሀም፣ ክሪስታል ፓላስ እና አቶን ቪላ ጥቂት ገንዘብ ወጭ ያደረጉ ሆነዋል፡፡ ቼልሲ ከተጫዋቾች ሽያጭ 226.7 ሚሊዮን ፓውንድ በማግኝት ቀዳሚው ሲሆን ማንችስተር ዩናይትድ እና ፉልሀም ከሽያጭ ምንም አይነት ገንዘብ ማግኝት ያልቻሉ ክለቦች ናቸው፡፡
በአንተነህ ሲሳይ